Thursday, July 24, 2014

“Those who do not move, do not notice their chains.” ― Rosa Luxemburg

አንድ ለአምስት የወያኒቱ የስለላ ድር በዲያስፖራ (ከኢትዮሚዲያ የተወሰደ)

ይድረስ እንደ እኔ ከወገን ዘመዳችሁ ከሞቀ ቤታችሁና ከምትወዷት ሃገራችሁ ሳትወዱ በግድ እንጀራና ነጻነት ፈልጋችሁ ለተስደዳችሁ ኢትዮጵያዊ ወገኖቼ፡፡ በኔና እንደ እኔ ከሁለት ያጣ ሆነን ጭንቀቴንና እየደረሰብን ያለውን ከፍተኛ ችግር ለናንተ ላዋያችሁ በውስጤ እንደ ሰደድ እሳት የሚቆጠቁጠኝን ችግሬን ላካፍላችሁ ወገኖቼን አስቸግሬ ወደ እናንተ እንዲያስተላልፉልኝ ቆርጬ ስነሳ አብረውኝ በነበሩ ሌሎች ወገኖቼም ሆነ በራሴ ጉዳት እንዳይደርስ በመጨነቅ የማወጋችሁ አሳዛኝ እህታችሁ ነኝ፡፡ እኔ ሳላውቅ የገባሁበት ችግር ውስጥ ሌሎችም ብዙ ወገኖቼ ክብደቱንና መዘዙን ስይገባቸው የሃገራችን ጠላት የወያኔይቱ ተላላኪዎች እየተጠቀሙባቸው ስለሆነ ላስጠነቅቃቸው ፈልጌና የራሴንም ሃጢያት እግረመንገዴን ለመናዘዝ ናው፡፡

ምርጫ 97ትን ተከትሎ በወገኖቼና በቅርብ ዘመዴ ላይ በደረሰው ግድያ ምክንያትና ተደናግጬና ተስፋ ቆርጬ ትምህርቴን
አቅዋርጬ የተሻለ ህይወትም ጭምር ፍለጋ ከሌሎች ጓደኞቼ ጋር ወደ አረብ ሃገር ተሰደድኩኝ፡፡ ብዙዎቻችሁ እንደሰማችሁትና
አንዶአንዶቻችሁም ደርሶባችሁ እንደምታውቁት ዘግናኝ የስቃይና የባርነት ህይወት ለአራት አመታት ተሰቃይቼ በፈጣሪ ፈቃድ ወደ
አውሮፓ ጠፍቼ ስደርስ በህይወት እንድንኖር ፈጣሪ የፈቀደልን ብቻ ነበርነ ለጊዜውም ቢሆን ሰላም ሃገር የደረስነው፡፡ በዚህ የፈተና ጉዞ ከረሃቡና የበረሃው ጉዞ ስቃይ በተጨማሪ በማንም የግመል እረኛና የስደተኛን ንብረት በመዝረፍ የጠገቡ አመላላሽ ነጋዴዎች ንብረታችንን ብቻ ሳይሆን የነበረንን የሰውነታችንን ክብርና እየተፈራረቁ በወንድሞቻችን ፊት ብዙ አሳፋሪ ለመናገር እንኳን የሚሰቀጥጥ ግፍ ተፈጽሞብናል፡፡ ወንድሞቻችንም እንደኛው የያዙትን ንብረትና ጥሪት ተገፈው እየተደበደቡ ደክመው ህይወታቸው ያለፈና በየበረሃው ካለቀባሪ አሸዋ በልቶ ያስቀራቸው ባህር ላይ ለአሳ ነባሪ የገበርናቸው ጥቂት አልነበሩም፡፡
 ከዚህ ሁሉ ስቃይ ቦኋላ ፈጣሪ ይብቃሽ ብሎኝ የተጠለልኩበት የመጀመርያ የስደት ሃገር ወገኔ የወንዜ የሃገሬ ልጅ ነች ብዬ እውነተኛ ማንነቴንና አረብ ሃገር የት እሰራ እንደነበር ያጫወትኳት ተንኮለኛ ሚስጥሬን ካወቀች ቦኋላ ነበር ማንነቷን የተረዳሁት፡፡ ከብዙ መቀራረብ ቦኋላ ችግሬንና የውስጥ ሚስጥሬን ጠንቅቃ ከተረዳች ቦኋላ አዛኝ መስላ ለማንኝውም ወደ ሃገርሽ ቢመልሱሽ ችግር እንዳይገጥምሽ ወደ ተቃዋሚዎች እንዳትቀርቢ፡፡ እዚህ ከሚኖሩ የመንግስታችን ደጋፊዎች ጋር አብረሽ ከተደራጀሽ ምንም ክፉ ነገር ቢደርስብሽ ጥለው አይጥሉሽም ብላ ሳትጨርስ ነበር አንቀጥቅጦኝ ዘልዬ አንገቷን ያነኳት፡፡ ጸጉሯን ጨምድጄ ሁሉ ያፈሰሳችሁት ደም ሳይደርቅ እዚህ ነጻ ሃገር ድረስ ተከተላችሁኝ ወይ? ብዬ እንዳበደ እየጮህኩኝ በጥርሴ ልዘለዝላት ስታገል ነበር የመጨረሻ የማስታውሰው፡፡ እብድ ናት ተብዬ እጅ እና እግሬ በካቴና ከአልጋዬ ጋር ተጠፍሮ ነበር የነቃሁት፡፡ ምን እንደወጉኝ ባላውቅም ከዚያን ጊዜ ወዲህ የሚያፈዝ እንቅልፍ የሚያበዛና የሚጫጫን ነገር ጥሎብኝ አልፎዋል፡፡

 ሲሻለኝ ስደት የጠየኩበት መስሪያ ቤት ዋስ ሆኖ መሰለኝ አስፈትቶኝ ወደ ነበርኩበት ካንፕ ሲመልሰኝ ይቺው ወያኔይቱ አሁንም
ሳታፍር ቀርባኝ አረብ ሃገር ድረስ ተጻጽፋ እዛ በሚኖሩ ዘመዶችዋ አማካይነት አሰሪዎቼን ተገናኝታ ባልጠበኩት መንገድ የፓስፖርቴንና የስራ ኮንትራት ፎቶ ኮፒ ቅጂ በእጇ እንዳለ አሳየችኝ፡፡ የጠየቀችኝን ባልተባበር ዶኪሜንቱን ለፖሊስና ለስደተኛ ክፍል እንደምታስረክብና ዲፕርት ተደርጌ ከቦሌ አየር ማረፊያ መንግስት ተቀብሎ ምን ሊደርስብኝ እንደሚችል ስትዘረዝርልኝ የታየችኝ እናቴ ዘንድ አደራ ያስቀመጥኳት ጨቅላ ልጄና ከሃገር መውጫ ቪዛ ተበድራና ንብረቷን አስይዛ የላከችኝ እናቴን ነበር ያስታወስኳት፡፡ እያለቀስኩኝ እህት አለም እንኳን የመንግስት ደጋፊ የፈለግሽውን አድርጊኝ እተባበርሻለሁ እባክሽ ኬዜን አታበላሺ ብዬ ነበር እግሯ ላይ የተንከባለልኩት፡፡ ያበላሸሁትንና የነጨሁትን የአርቲፊሻል ጸጉር ከነመቀጫው አራት መቶ ዶላር ከፍዬ፡ አንድ ለአምስት በሚባል ትንሽ ማህበር እንድደራጅ እራስዋን ጨምሮ ሌሎች አራት ሰዎች እዛው አብረን የምንኖርና በፍጹም ጠርጥሬ የማላውቃቸው ሰዎች አስጠኗት ብላ አገናኘችኝ፡፡  አንዳንዶቹ እንደ እኔው ግራ የገባቸውና የማያምኑበትን ተገደው የተቀበሉ እንደሚያስመስሉ ብጠረርም እርስ በእርስ እንድንፈራራ እሷ በሌለችበት ያወራነውንና ያደረግነውን ለየብቻ ሄደው ስለሚነግሯትና ይህንንም እሷ እየመጣች እከሌ የደበቀኝን እከሊት ነገረችኝ እያለች እርስ በእርሳችን እያወጣጣች ስለምታጋጨን አንተማመንም፡፡ መንግስታችንን የሚቃወሙ ጸረ ሰላምና ጸረ እድገት የሆኑ የደርግ የኢሕአፓ እና የቅንጅት ርዝራዦች ናቸው አትመኗቸው ካገኟችሁዋቸውም ምን እንደሚሉና ምን እየሰሩ እንደሆነ ለቡድናችን ሪፖርት አድርጉ ትለናለች፡፡ እንደ አጋጣሚ ሰው ካላገኘንና የምናስተላልፈው ሪፖርት ከሌለ በጸረ ልማቶች እንደተወናበድንና ሚስጥር መደበቅ እንደ ጀመርን ሌላ ሪፖርት እንደደረሳት ስለምታስፈራራን ከዚህ ሁሉ ስቃይ ለመውጣት ያልሆነ የሆነውን ወሬ እየነገርናት ከስቃይ ለመዳን እንሞክር ነበር፡፡ ይህ ህይወታችንን ለማትረፍ በወገኖቻችን ላይ ጀርባችንን አዙረን ህዝባችንን ከሚበድሉ ጎን መሰለፉ ውስጤን እየቆጠቆጠው ቢሆንም ነብሴ ስላሸነፈቺኝ ስተኛ ሁሌ አለቅሳለሁ፡፡ በውስጤበራሴ ላይ መተማመን ከመምከኑም በላይ የሚታገሉ ተቃዋሚዎችን ሳይ መጥላ ጀመርኩኝ፡፡  ፈጣሪዬ ሊቀጣኝ መሰለኝ ይህንን ሁሉ ስህተት ተሳስቼም የተጠለልኩበት ሃገር ለመሰደድ የሰጠሁትን ምክንያት ስላልተቀበለኝ ወደ ሁለተኛውና አሁን ያለሁበት ሃገር በዚችው ሴትዮ በምታውቃቸው ሰዎች እርዳታ ገባሁ፡፡ የፈራሁት እውነት ሆኖ ተቀብለውኝ ያረፍኩበት ቤት፣ የስደት መጠየቂያውን መንገድ መንገዱን የሚመክሩኝና ኤርትራዊ ነኝ ብዬ እጄን እንድሰጥ ኬዝ የሚያስጠኑኝ እነዚሁ ከሃገር ያሰደደኝን መንግስት የሚደግፉ ጉዶች መሆናቸው ነገሩን ሁሉ ቅጥ አስጠፉብኝ፡፡ በተለይ ዋሽተው የሚረዱኝ ምክንያት ጸረ ልማቶችንና የድሮ ስራት ናፋቂዎችን እንደምቃወም በተላለፈልን መረጃ መስረት ነው እያሉ ያላሰብኩትና ያልጠበኩት ችግር ውስጥ ስለዶሉኝ ነገር ሁሉተዘበራርቆብኝ ውሉ ጠፋብኝ፡፡ እንደማልደግፋቸውና እንደምቃወማቸው ልነግራቸው እየፈለኩኝ ነፍስና ስጋዬ ብቻ ሳይሆኑ የኔን እርዳታ የምትጠብቀው ህጻንና፣ ንብረቷን አስይዛ ለፓሳፖርቴና መጓጓዣ እዳ የገባችዋ እናቴ አሳዘኑኝ፡፡ ይህንን የምነግራችሁ እንድትራሩልኝና ጥፋቴን እንድታሳንሱት አይደለም፡፡
 ክፉ ለሰራ ፈጣሪም ስለማይተባበረው ይሄ አዲስ የመጣሁበት ሃገር ኤርትራዊ መሆኔን ካለመቀበላቸውም ሌላ በጥያቄና መልስ ጊዜ
ብዙ ነገር ስለተበላሸብኝ የስደት ጥያቄዬ ተሰርዞ ወደ ሃገራችሁ እንመልሳችኋለን ተብለን አንድ ካንፕ ውስጥ ወደ ሃገሬ እስክመለስ
በጊዜያዊነት ያጉሩኛል፡፡ የተባለው ካንፕ ውስጥ ደርሼ ሱባኤ ገብቼ ለሰራሁት ሃጢያት እስከምመለስ እጸልያለሁ ብዬ ወሰንኩኝ፡፡
እንደደረስኩም ከማንም ላለመቀራረብ ወሰንኩኝ፡፡ በተለይ ማን ምን እንደሆነ መለየቱ ስለሚከብድ የሃገሬን ልጅ ሸሸሁ፡፡ተመሳሳይ ችግር እንዳይገጥመኝ መጠንቀቅና መደበቅ ጀመርኩኝ፡፡ ለሊትና ቀን አልጋዬ ላይ አሞኛል ብዬ ቤቴን ቆልፌ ማልቀስ ሆነ ስራዬ፡፡ ለጥቂት ቀናት ከሰው ብሸሽም እንደፈለኩትና እንደተመኘሁት አልሆነልኝም፡፡ ባልጠበኩትና ባላሰብኩት መንገድ ስልክ ይፈልግሻል ተብዬ አንዲት አይቻት እንኳን ከማላውቃት ሴት በሬን ቆርቁራ የእጅ ሞባይሏን አቀበለችኝ፡፡ በማላውቀው ሰው ሞባይል ማን ይደውልልኛል ብዬ በመገረም ቀስ ብዬ ማዳመጥ ጀመርኩኝ፡፡ አዎ ያቺ መጀመርያ የቀረበችኝ ሃይለኛ ልጅ ከመጀመርያው የስደት ሃገር በስልክ ለወያኔዎቹ እንደ የገዛችው እቃ ልታረካክበኝ ነበር የደወለችው፡፡ የተቀበሉኝ ሰዎች የደረሰብኝን ሁኔታ ተከታትለው እስከ አዲሱ አድራሻዬ ነግረዋታል፡፡

የአዛኝ ቅቤ አንጓች ሁና ልታጽናናኝና አሁን ያለሁበት ካንፕ ከሚኖሩ ማህበርተኞቼ ልታገናኘኝ መሆኑ ነው፡፡ እዛ ካምፕ መምጣቴ
እንደነገረቻቸውና እንደሚረዱኝ አስረዳችኝ፡፡ የነሱ አባል በመሆኔ ምክንያት ስሜ ለኤንባሲ እንደተላለፈና ሊያስወጡኝ ቢፈልጉ የመጓጓዣ ሰንድ ባለመስጠት እንደሚተባበሩኝ አብራራችልኝ፡፡ መንግስታችን አናውቃትም አንቀበላትም ብሎ ካልተባበረ የመኖርያ ፈቃድ በግድ እንደሚሰጡኝ ስትተነትንልኝ በፍርሃትና በድንጋጤ የሟሸሽኩትን እንደገና ነብስ ዘራችብኝ፡፡ ለካ ሳላውቀው የወያኔ ድርጅት አባል እንደሆንኩኝ ተነግሯቸው ኑሮ እንኳን ደህና መጣሽ ብለው ሁሉም ይስሙኝ ጀመር፡፡ እሸሻቸዋለሁ ያልኩትን ረሳሁት፡፡ ሲሞቅ በማንኪያ ሲቀዘቅዝ በእጅ እንዲሉ፡፡ አይዞሽ እኛም እንዳንቺ መጀመርያ ግራ ተጋብተን ነበር ቦኋላ ነው መንገድ መንገዱን እዚህ የቆዩ ሰዎች ያሳዩን፣ ነገ እዚህ ፈቃድ ያላትን ዋናዋን የማህበራችንን ሃላፊ እረዳታችንን መምጣትሽን ስለሰማች ቤትዋ ወስደን እናስተዋውቅሻለን አሉኝ፡፡ ሃገሬ ውስጥ ያለሁኝ ነበር ሁኖ የተሰማኝ፡፡ ከሃገር ሃገርና ከካንፕ ካንፕ ሲቀባበሉኝ ዓለሙን በሙሉ የገዙት ነበር የመሰለኝ፡፡ አረብ ሃገር ሁኜ አዳምጣቸው የነበሩ ሁሉ የተቃዋሚ ድርጅቶችና ተከታዮቻቸው ለካ በፓልቶክና በፌስ ቡክና በድህረ ገሳች ላይ ብቻ ናቸው እስከማለት ነበር የደረስኩት፡፡ ለመኖርያ ፈቃድ ብዬ የገባሁበት አንድ አምስት ብሎ ነገር በተሃገሩና በመጠለያ ጣቢያው እንደ ጥላዬ እየተከተለኝና እንደ የሸረሪት ድር ዙርያችንን ላይ እየተጠመጠመ ነው፡፡ ህግና ስልጣኔ ያለበት ነጻ ሃገር አንዲት ትግሬኛ ተናጋሪ አስተባባሪያችን ይህንን ሁሉ የሰው ልጅ እንደ በግ እየነዳች እንደ ባርያ እያዘዘችን በጸረ ልማትና የድሮ መንግስት ናፋቂ ደርጎች ስም ስንቶቹ ወገኖቻችንን እየሰለልንና ስማቸውን እያበላሸን እንደነበር ሳስበው ይሰቀጥጠኛል፡፡

የተደላደለ ህይወት ያላት አለቃዪቱ ቤት ተሰብስበነ ስታስተናግደን አንዲትም ጊዜ ወያኔይቱን የማይደግፉትን ስደተኞች ተቃዋሚ
የሚል ቃል ስትጠቀም አልሰማሁም፡፡ ስም ወደ ጸረ ልማት ጸረ የአባይ ግድብ አሸባሪዎች የእስላም አክራሪዎች ተቀይሯል፡፡
በመጨረሻው የተጠለልኩበት ሃገር በሁለት የተለያየ የመጠለያ ካንፕ ቆይታዬ እንደ እኛ አንድ ለአምስት ተደራጅተው ወያኔይቱን
ከሚደግፉ ሰዎቻቸው ጋር ተዋውቄያለሁ፡፡ በየቦታው ከላይ ሆነው የሚያዙን የሰሜኑ ወገኖቻችን ይሁኑ እንጂ ከአስር ዘጠኝ እጅ እንደ እኔ ከሌላ ክልል የመጡ ናቸው፡፡ ጊዜው ከፍቶ በእንጀራው እየመጡበት ወገኑን መክዳትና አሳልፎ መስጠት የተለመደ ሆንዋል፡፡ የወያኔይቱ ስም በመንግስታት እንዳይወቀስ ኤርትራ ብላችሁ ስጡ የሚለው ተንኮል የገባኝ ኋላ ነው፡፡ የግለሰቡ ኬዝ ቢፈልግ ይበላሽ እንጂ አዲስ እጅ ያልሰጠ ሰው ሲመጣ የሚመከረው ኤርትራዊ ነኝ ብሎ እጅ እንዲሰጥ ነው፡፡ በእርግጥ በዛ መንገድ ፈቃድ ይቀላል ተብሎ ቢታመንም ዋናው ምክንያት ግን ወያኔይቱ በመንግስታት ወቅሳ እንዳይደርስባት ጭምር እንደሆነ ቦኋላ ከተቃዋሚዎች ሰምቻለሁ፡፡ ለነገሩ እንኳን ትግሬዎቹ እኛ በሙሉ ኤርትራዊ ሆነዋል፡፡ የእውነት ኤርትራውያኖቹም ግራ ገብታቸው ነው መሰል ከኛ ጋር አንድ ለአምስት መደራጀት ጀምረዋል፡፡ ለምን ያኔ እንዳስገነጠሏቸው እንጃ፡፡ ከኛው ጋር የመንግስት ተቃዋሚ የሚባሉትን ስም ያጠፋሉ፡፡ የሚሰሩትንና የሚናገሩትን ቀርቶ መሬት ላይ ጥብ ያለውን እየሰለሉ ሹክ ይላሉ፡፡ እነዚህ ብኩኖች ጓደኛ ዘመድ ትዳር ሚስት የማያውቁ ድንበር የለሽ ጉዶች ናቸው፡፡ ከቤተ ክርስቲያን ከእስፖርት ከህዝብ ስብሰባ ከተጋበዙበት ቤት ሲመለሱ እንዴት እንደነበር የተፈሳው አይቀራቸውም፡፡ ለመታመን ብለው አብረው የሚበሉ የሚጠጡትን ሁሉ ይሰልላሉ፡፡ አስላዮቹ እንኳን ይገምቱናል ብለው የማያፍሩ ለፍርፋሪ የተንበረከኩ ሃገር አሰዳቢዎች ብዙ ናቸው፡፡ እኔንም አሳስተውኝ ነበር፡፡በተለይ እኛ ሴቶችን አለቃይቱ ከበላይ ምን ስትታዘዝ እንደሆን እንጃ ስልኪቷን በጠዋት ታቃጭልና አሁኑኑ አንቺና እከሊት አትራክቲቭ ሁናችሁ ስልክ ሳትደውሉ በቀጥታ እከሌ ቤት ሄዳችሁ በዚህ ስናልፍ ሰላም ልንልህ ነው ብላችሁ ግቡ፡፡ ስትደርሱ ምን ይሰራ እንደነበር አጥኑ፡፡ኮኒፒዩተር ላይ ከነበረም ምን ያነብ ወይም ይጽፍ እንደንበር አስተውሉ፡፡  የሆነ ነገር በኮንፒዩተር አሳየን ብላችሁ ሲከፍት የፓልቶክ ስሙን ለማየት ሞክሩ፡፡ ሻይ ቡና ሊላችሁ ወደ ኩሽና ሲገባ ጠረጴዛው ላይ ማስታወሻ ደብተር ወይም ብጣቂ ወረቀቶች ላይ የምታዩትን ስም አድራሻ ስልክ ቁጥር ለማስታወስ ወይም በጽሁፍ ለመያዝ ሞክሩ፡፡ ሌላም ጠቃሚ ነገር እንደ ዩአኤስቢ ካኛችሁ ውሰዱ፡፡ በሴትነታችሁ ተማርኮ የሚቀባዥረውን ከቻላችሁ በሞባይል ቅዱት፡፡ የማያስተውል ከሆነም ወደ መጸዳጃ ቤት ሄዳችሁ ምልክት ስጥታችሁኝ አሰሙኝ፡፡ ለፍቅር ለመቅረብ የሚፈልግ ከመሰላችሁ አደፋፍሯቸው
እንጂ እንዳይሸሽዋችሁ ፊት አትንሷቸው፡፡ ስትመለሱ ቡና እየጠጣን እያንዳንዱን እንቅስቃሴ እንጫወታለን፡፡ ለወደፊቱ መሻሻል
የሚገባውንም እንዲሁ እንጫወታለን፡፡ይህንን ጸረ ልማትና ጸረ አባይ አቅዋማቸውን ካልቀየሩ አንድ ቀን በእጥፍ ናስከፍላቸዋለን
ትለናለች፡፡ ኧረ ስንቱን ነግሬ ልጨርስላችሁ፡፡ ወሬ ካላመጣንላት ትግሉን እርግፍ አድርጋችሁ ትታችሁታል፡፡ እናንተ ተኝታችሁአሸባሪዎች እየተጠናከሩ ነው ለሃገራችሁ ስትታገሉ አትፍሩ፡፡ መንግስታችን ብዙ ወገኖቻችንን መስዋእት አድርገው ነው ከአንባ ገነን ወደ ልማታዊ መንግስት የመሰረቱልን፡፡ እናንተ ግን የምትረቡ አትመስሉም፡፡ ኤንባሲዎች እንዳትመለሱ ለሚተባበሯችሁ እንኳን ውለታ ለመመለስ የምትሳሱ አድር ባዮች ናችሁ፡፡ ኧረ ስንት አይነት የስድብ መአት ? እንዲያውም ትንሽ ወይን ቀማምሳ ያደረች ቀን ያስታውቅባታል እንደ የቀጠረችን ገረድ እንጂ እንደ ሰው አትቆጥረንም፡፡ የኛ የሴቶቹ ቀርቶ አሳማ ከነብሱ ውጠው የወፈሩ የሚመስሉ ወንዶች ከኛ ብሰው የአውራ ጣት ለምታክል ሴትዮ ወኔያቸው ፈሶ ወሬ በስልክ ወሬ ሲያመላልሱላት መስማቱ ያሳዝናል፡፡ እኔማ አንዳንዴ ምነው የአረብ ሃገር አሰሪዬን ጭነቅላቴን እየኮረኮመችና በጥፊ እያጠናገረችኝ የምትጮህብኝን አሰሪዬን እየመሰለችኝ መታነቅ የማስብባቸው ቀናት ብዙ ናቸው፡፡

በዚህ ሁኔታ ላይ ሆነን እኔም በስለላዬና የሰላማዊ ስደተኞችን ስም በማጥፋትና ደካማ ወንዶችንም በሴትነቴ ከጎልበቴ በላይ
እየለብበስኩ ወያኔይቱንና እስዋ ካንፕ ውስጥ የሾመችልንን እያገለገልኩኝ ስልከሰከስ አንዲት የተባረከች ቀን ደረሰች፡፡ አለቂቱ በሞባይሌ ታቃጭልልኝና እንደተለመደው አሁኑኑ ያቺን ሴክሲ አለባበስሽን በደንብ አሳምረሽ በቅርብ ጠበቃሽ የላከልሽን ደብዳቤ ይዘሽ ነይ ትለኛለች፡፡ ወቅቱ በጣም የብርድ ጊዜ ስለነበር ሁሌ እንደማደርገው ከጉልበት በላይ መልበሱ ቀርቶ ብርዱ ተለብሶም አይቻልም፡፡ የሰውነቴን ቅርጽ በደንብ የሚያሳይ ልብስ ለብሼ ወፍራም ኮቴን ከላይ ደርቤና የእጅ ጋንቲዬን አጥልቄ በቅዝቃዜው እየተንቀጠቀጥኩኝ ቤቷ ደረስኩኝ፡፡ ሃገሩን እንደሚወድና ወያኔይቱን እንደሚቃወም ቀድሞም ልቤ ይጠረጥር የነበረና አሁን በትክክል የተረዳሁት ወገኔ ቤቱ ሄጄ የበሩን ደወል እንዳቃጭልና ከጠበቃዬ የተጻፈልኝን የማውቀውውን ደዳቤ እንዲተረጉምልኝ ለመግቢያ ምክንያት እንዳደርግ ትነግረኛለች፡፡ አንዴ እቤት ከገባሁ ቦኋላ ፍቅር ከመስራት በስተቀር በደንብ እያጫወትኩት እንዳዝናናው አስረድታኝ አንዳንድ ጥያቄ እንድጠይቀው ትንነግረኛለች፡፡ ተቃዋሚዎችን መተባበር ብፈልግ የቱ ነው ጥሩ? አላማቸው ምንድነው? ለስደተኛ ስንት መዋጮ ታስከፍሉኛላችሁ? የሚለውን እየጠየኩኝ በስልክ እንድቀዳው በደንብ አሰናድታ ላከችኝ፡፡ ይህ ሰው ምን አቅዋም እንዳለውና የማን ተቃዋሚ አባል እንደሆነ ማወቅ የተቸገረች ብቻ ሳይሆን ፊት ስለሚነሳት ጠንዳ ይዛዋለች፡፡ እንደ ሌሎቹ ደካማ ወንዶች ለሴት ሲለሳለስ ሰዎች ስብስባ ስሙትማ ይህንን ተቃዋሚ ነኝ ባይ እያለች ስም ልታስቅበት ነው የተጣደፈችው፡፡ደጋግማ ስለ ትቢቱ ስታወራ ስለሰማሁ በኔ በኩል ልታጠምደው እንደሆነ ገብቶኛል፡፡ እስካሁን እኔን አልደፈረችኝም እንጂ አንዳንዶቹን ለጎረምሶች እንደምታቃጥራቸው ሰምቻለሁ፡፡
 እንዳገኘው የላከቺኝ ሰው አንድ ቀን በራፉ ላይ ቆሞ ከኔ ጋር የነበረ ልጅ ጋር አግኝተነው ስንተዋወቀው አዲስ መሆናችንን ስንነግረው የስልክ ቁጥሩን ሰጥቶን ነበር፡፡ እቤት ገብታችሁ ቡና ልጋብዛችሁ ሲለን አሁን እንቸኩላለን ብለን ሌላ ጊዜ እንመጣለን ብለን ነበር የተለያየነው፡፡ እውነተኛ ምክንያታችን ግን የአባይን መገንባት የሚቃወም ጸረ ልማት ነው ብላ ሴትዮይቱ ስላስጠነቀቀችን ችግር ውስጥ እንዳንወድቅ ነበር፡፡ የዚያን ቀን ከኔ ጋር የነበረውን ልጅ ሸኝቼው ተሸሽጌ ተመልሼ ችግሬን ባወራው ልቤ ፈልጎ ነበር፡፡ ግን ፈራሁ፡፡

ለመጀመርያ ጊዜ ስለነበር ነበር ብቻዬን እንድሄድ የፈቀደችልኝ ትንሽ ነጻነት ተሰምቶኛል፡፡ እቤቷ ስብስባን በወያኔና ደርግ መሃል
ያካሄዱትን የጦርነት ፊልም ጭንቅላታችን ውስጥ እየጠቀጠቀች ልታሳብደን ከደረሰው ይሄ ይሻለኛል፡፡  በተነገረኝ መሰረት እጄ እየተንቀጠቀጠ የበሩን ስልክ ተጭኘው ስጠብቅ በሩን ከፍቶ በእጁ ሰላምታ ሰጠኝ፡፡ እየተንተባተብኩኝ የጠበቃዬን ወረቀት እንዲተረጉምልኘ እንደሆነ የመጣሁት ነገርኩት፡፡ ግቢ ብርድ ነው ብሎኝ የምንቀጠቀጠው በብርዱ ብቻ መስሎት
ማሞቅያውን ከፍ አድርጎ ጋቢ አመጣልኝ፡፡ ሻዩን ጥዶ የሃገሩን ቋንቋ እሱም ያን ያህል እንዳልሆነ አስረድቶኝ ከሞላ ጎደል የማውቀውን ደግሞ ተረጎመልኝ፡፡ ርህራሄውንና ሊረዳኝ የሚያደርገውን ትብብር ሳይ ያቺን ሰይጣን አለቃችንን ብቻ ሳይሆን እራሴንም ጠላሁኝ፡፡ የዋህነቱ ቅንነቱና ወገኑን ለመርዳት የሚያደርገውን ሙከራ ስገነዘብ በእውነት ስንት የሃገሬ ልጆች እንደበደልኩኝ ተሰምቶኝ ተንዘፍዝፌ ሳላውቀው እንባዬ በአራት ማእዘን መውረድ ጀመረ፡፡ ያገሬ ልጅ ተደናግጦ መሃረቡን አውጥቶ አዝኖልኝ የረጠቡ አይኖቹን ባንድ እጁ እያሻሸ አይዞሽ ይሄ ቀን ያልፋል ሁሉም መጀመርያ ተቸግሮ ነው እያለ ትከሻዬን እያሻሸ ሲያጽናናኝ ባሰብኝ፡፡ ከዘመዶችሽ የሰማሽው አዲስ ነገር አለ ወይስ ኬዝሽ ነው ያበሳጨሽ ብሎ አይን አይኔን ሲያይ አይኑን ፈራሁት፡፡ ለምን እንደመጣሁ እንደበፊቶቹ ሰዎች መድፈር አቃተኝ፡ ፡ በጭንቀት ሰውነቴ ውስጥ የነበረው ብርድ ወደ ሙቀት ተቀይሮ እጆቼን ሲረጥቡና በጀርብዬ ላቤ ሲከባለል ይበልጥ የሚያውቅብኝ መስሎኝ ልሳኔ ሁሉ ተዘግቶ በድን ሆንኩኝ፡፡ ፊቴን ለመተጣጠብ ወደ መጸዳጃ ቤት ገብቼ በሩን ቆልፌ በለቅሶ ያበጡ አይኖቼንና ፊቴን ስመለከት የወንጀለኛነት ስሜት ተሰምቶኝ እራሴን ማየት ጠላሁ፡፡ ገንዳው ጫፍ ቁጭ ብዬ ስንሰቀሰቅ ሰምቶኝ ኑሮ ነይ ብቻሽን አይደለሺም አይዞሽ ሲለኝ አንድ አፍታ ያቺ ሰይጣን የመጀመርያ ሴቲቱ ስልክ ደውላ አይዞሽ ብቻሽን አይደለሽም ያለችኝን አስታውሼ አረርኩኝ ደበንኩኝ፡፡ ከዚህ የተሻለ አጋጣሚ አላገኝም ብዬ የምሰራውን ሁሉ ልዘረዝርለት ወሰንኩኝ፡፡ በዚህ መሃል ስልኬ አቃጨለ፡፡ ቁጥሩን ሳየው የዛች ሰጣን ስለነበር ተደናግጬ በስልኩ የምታየኝ መስሎኝ ስልኩን መሬት ላይ ለቀኩት፡፡ ስልኬ ተባበረኝ መሰለኝ ባትሪውና ስልኩ ተለያይተው እዛ ሲቢንቶ ላይ ተከሰከሱ፡፡ ሳነሳው መስታውቱ እዛው ላይ ደቆ ስባሪው አውራ ጣቴ ላይ ተሸንቁሮ ደሜ
ኮለል ብሎ ወረደ፡፡ ቀኑ አስራ ሁለት የሚካኤል ቀን ስለነበር እዛች ሽንት ቤት ውስጥ ጥፋቴን በእራሱ መንገድ እያሳየኝ እንደሆን ገባኝ፡፡ ደሙ አልቆም ስላለኝ በሩ ላይ ሆኖ ለሚያጽናናኝ በሩን ከፍቼ ገንዳው ቧንቧውን ከፍቼ በጣቴ የሚደማውን ይዤ ማልቀሴን ቀጠልኩኝ፡፡

 ምኑንም ያላወቀው ያገሬ ልጅ ተደናግጦ እራፊ ጨርቅ አምጥቶ ጠቅልሎ አስሮልኝ የተበታተነውን ስልክ ሰባስቦ ወደ የእንግዳ
መቀበያው ይዞኝ ገባ፡፡ ብስጭት ያስረሳል ብሎ ወይን ቀድቶልኝ አጠገቤ ተቀምጦ እንደ ታላቅ ወንድም ትከሻዬን እያሻሸ የሚረብሽሽ ነገር ካለ ለመስማት ዝግጁ ነኝ ጤናሽስ እኔት ነው ያምሻል ወይ ሲለኝ ከባድ በሽታ እንደያዘኝ የጠረጠረም መሰለኝ፡፡ ለኔ የምትነግሪኝ ለቄስ እንደምትነግሪው አድርገሽ ውሰጅው ሲለኝ የማስበውን ሁሉ ያወቀብኝ መሰለኝ፡፡ ጣቶቼን እያፍተለተልኩኝና ጥርሶቼ እየተንገጫገጩ ልሰልለው እንደተላኩኝ ነግሬው ወደ በሩ ለመሮጥ ቃጣኝ፡፡ ምንም የመገረም ስሜት ሳያሳየኝ የሰይጣኗን ስም በቀጥታ ጠርቶ እሷ ነች አንቺንም የላከችሽ? አለኝ፡፡ እንዴት አወክ? ሌሎችስ እንዳሉ ማን ነገረህ? ብዬ እሱኑ ፈርቼ በእንባ የቀሉ አይኖቼን አፍጥጬ መልስ በፍጥነት መስማት ፈለኩኝ፡፡ ያጋመስኩትን ወይን እየሞላው ቀስ በይ አትቸኩይ፡፡ ወያኔ በየስርቻው የስደተኞችን ችግር በመጠቀም ወደ ተቃዋሚ ሰፈር ገብተው እንዳይታገሉ በጀት መድበው አንድ ለአምስት እያሉ የምታሰባስባቸውን እንሰማለን እናውቃለን፡፡ ብዙዎቹምከሃገር ውስጥ ተመልምለውና ተመክረው ሰልጥነው የሚመጡ ናቸው፡፡ አንቺ እንዳለሽበት ጊዜያዊ ካንፕ ደግሞ ወደ ሃገር ሲመለሱ እንደሚፈሩ ወያኔ ስለምታውቅ ሆዳሙን በጥቅም ፈሪውን ስም እያስጠፋችና እያስፈራራች እየመለመለቻቸው እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ዋናው የወያኔ እቅድ የተቃዋሚውን ሰፈር ከፋፍሎ ለማዳከምና ተሰሚነት ያላቸውን ግለሰቦች በመነጠል አንገታቸውን ለማስደፋት ነው፡፡ እኛም ለችግር ብለው የሚጠጓቸውንና ለጥቅም ብለው ወደ እነሱ እየተጠጉ ስደተኛውን የሚሰልሉትን ለይተን ብዙዎቹን እናውቃለን፡፡
አንቺን እንድትሰልዪ እንደላኩሽ ተቃዋሚውም እንደ አቅሙ እንዳንቺ ተቸግረውና ተገደው በተመለመሉና ወገናቸው ምንም ውስጥ ሆነው መርዳት በሚፈልጉ ሃገር ወዳዶች ውስጣቸው አዘጋጅተን እንከታተላለን፡፡ ስለ አንቺም ሆነ ስለሌሎቹ ሰምተናል፡፡ብሎ ምንም የማያውቁት ጉዳይ እንደሌለ እውነት የሆነ ነገር ዘርዝሮ ሲነግረኝ ፈዝዤ ቀረሁ፡፡

 አንዴ ተሳስተሽ ከገባሽበት ጣጣ ውስጥ ለመውጣት አሁን እንደምትነግሪኝ ከነሱ መሸሽ ሳይሆን አንዴ ገብተሽበታል እዛው መቆየት ነው፡፡ እነሱ መስማት የሚፈልፈልጉትን እየነገርሻቸው እራስሽንም ሆነ ሌሎችን ላደጋ ሳታጋልጪ ከእኛ ጋር እየተመካከርሽ የተገላቢጦሽ እራሳቸው ላይ መስራት ይቻላል፡፡ በሰው ሃገር ውስጥ ተቀምጦ ስደተኛን መሰለልም ሆነ መጉዳት ከባድ ወንጀል እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ነገር ግን ብዙ መረጃዎችና ምስክሮች ማሰባሰብ አለብን፡፡ አሁን ተንኮሉ ገብቷቸው እንዳንቺ ወደ ወገን ሰፈር እየመጡ ያሉ ብዙ ናቸው፡፡ ይህንን ሁሉ ሚስጥርሽን ካወቁ ቦኋላ ወዲያው ብታስደነግጫቸው በስደተኛ ጥያቄሽ ሊጎዱሽ ይችላሉ፡፡ብሎ ብዙ ጠቃሚ እዚህ ልገልጸው የማልሻ ምክሮች መክሮ ሞራል ሰጠኝ፡፡ ባላሰብኩትና ባልጠበኩት መንገድ ወገኔን የምረዳበትና ሳላውቅና ሳይገባኝ ወገኔን ለግል ጥቅም ብዬ የከዳሁትን ማካካሻ መንገድ ከፍቶልኝ ለአንድ አመት ከሁለት ወር ከሌሎችም እንደ እኔ ተሳስተው ከነበሩ ጋር በሚስጥር እየተገናኝን የተቃዋሚውን ወገን ስተባበር ቆይቼ ፈጣሪዬም ታረቀኝ መሰለኝ የመኖርያ ፈቃዴ ተስተካከለልኝ፡፡ በየካንፑ ለቀሩት ጓደኞቼ ደህንነት ስል ዝርዝር ጉዳዩን ለጊዜው አልነግራችሁም፡፡ ነገር ግን እነዚህ ወያኔይቱን ሸሽተን መጣን ብለው ስደተኛውን የሚሰልሉና ይህንን ጨቋኝ
መንግስት የሚረዱትን በተለይ ዋናዎቹን በደንብ ተለይተው ይታወቃሉ ብዬ አምናለሁ፡፡

በሰው ሃገር ውስጥ ሆኖ ስለላ ማካሄድ ይቅርታ የሌለው ወንጀል ስለሆነ የሚመለከታቸው ሃገር ወዳዶች ከሃገሩ መንግስታት ጋር ሃገር ወዳዶችና የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች እየሰሩበት እንደሆነ አንዳን ፍንጮችና ውጤቶች እየታዩ ስለሆነ የሚጋለጡበት ጊዜ እሩቅ አይደለም፡፡ ምናልባት እንደ እኔ ሳታውቁ ወይም ለትናንሽ ጥቅማ ጥቅሞች ብላችሁ ህሊናችሁን ላቆሸሻችሁ በጊዜ እንደ እኔ ወገናችሁን በመርዳትና የመረጣችሁትን የተቃዋሚ ድርጅት በመተባበር የተግባር ንሰሃ ግቡ፡፡ በተለይ እናንተ ሃገር ውስጥ ወያኔይቱ በደለችን ብላችሁ የስደት ፈቃዳችሁን በማጭበርበር አግኝታችሁ አሜሪካና አውሮፓ አውስትራሊያ አፍሪካን ጨምሮ በመላው አለም የተደላደለ ኑሮ እየኖራችሁ ስደተኛን ለምትሰልሉበትና ለምትከፋፍሉበት ደሞዝ ሃገር ውስጥ የባንክ አካውንት ከፍታችሁ እንደሚከፈላችሁ ይታወቃል፡፡ በየቤተክርስቲያኑ ምእማናኑን የምትከፋፍሉ፡፡ በየፌስ ቡኩና በየየፓልቶክ ክፍሎች ስማችሁን እየቀያየራችሁ በወገኖቻችን ላይ ፍዳውን የምታራዝሙ ወደ ፊት በህግ ብቻ የምንፋረዳችሁ ሳይሆን እስከዛው ዘመድ ወገኖቻችሁ እንዲያውቁዋችሁ ትክክለኛ ስማችሁንና በመረጃ የደገፈ ስራችሁን በየተቃዋሚው ድህረ ገጾች ማውጣቱ ይቀጥላል፡፡ ወደ ሃገር በሚተላለፉ የየቴሌቪዥንና የራዲዮ ፕሮግራሞች ስማችሁ እንደሚወጣና ፎቶዋችሁ ተሰራጭቶ መቀጣጫ ትሆናላችሁ፡፡ ዘመዶቻችሁም ማንነታችሁን አውቀው ጥንቃቄ ይወዳሉ፡፡ከአሜሪካና ከአውሮፓ ሰርታችሁ ያመጣችሁት ንብረት ይመስል ከህዝብ እየዘረፋችሁ የምታከማቹት ንብረት ቤትና ንግድ እመኑን አትበሉትም፡፡ በየትኛውም ማእዘን ያሉ ጥቂት የማይባሉ ለሃገራቸው የሚቆረቆሩ ወገኖች እያንዳንዷን በህዝብ ደም የምታሰባስቡትን ንብረትና
ለምታደርሱት ጥፋት ይመዘግባል፡፡ ለዚህም የምትከፍሉት ዋጋ ከባድ ይሆናል፡፡ ከዚህ ከሚመጣባችሁ መአት ለመዳን ዛሬ ነገ ሳትሉና ሳታመነቱ እራሳችሁን የአንባ ገነኖች መጠቀሚያ ከመሆን ታቀቡ፡፡ ህዝባችን ይቅርታ አድራጊና መሃሪ ነው፡፡ በጥፋታችሁ ተጸጽታችሁ ቀኑ ሳይመሽ ወደ የህዝብ ጎራ መቀላቀል ይበጃችኋል፡፡ አሊያ ከማይቀረውና አድምኖ ከሚመጣው የሕዝብ የነውጥ ማእበል አትተርፉም፡፡ 

የህንን በእውነተኛ ድርጊት ላይ የተመሰረተ መረጃ በባለታሪኳ ፈቃድና ተባባሪነት ሲቀርብ ለባለታሪኳና ለሌሎች በሷ ሁኔታ ላይ ለሚገኙ ደህንነት ተብሎ የመዝጋቢውን ስም ጨምሮ ብዙ ነገር ተውጠዋል፡፡ የበለጠ መረጃ ለማሰባሰብ የሰዎችና የቦታወች ስም አልተካተቱም፡፡ ነገሩ በሂደት ላይ ስለሆነ አንድ አንድ የተነገሩ አሰቃቂ ተግባሮችን ለተለየ ምክንያት ተብሎ አንዳይጠቀሱ ሲደረግ ታሪኩ ተቀንጭቦ እንዲወጣ የተደረገው በባለታሪኳ ቁጭትና ግፊት ነው፡፡ ወደፊት ነገሮች መስመር ሲይዙ ታሪኩ ምንም ሳይቀነስና ሳይጨመር ከባለታሪኳ በቀጥታ ትሰሙታላችሁ፡፡ ለወገናችን መቆም ባንችል ስቃዩን ከሚያበዙበት ጎን አንሰለፍ፡፡

ሰላም ባዩሽ

Sunday, July 13, 2014

“It is the duty of youths to war against indiscipline and corruption because they are the leaders of tomorrow.” ― Ifeanyi Enoch Onuoha

ብስራት ደረሰ (ከአዲስ አበባ)

የፈሩት መድረሱ፣ የጠሉት መውረሱ ያለና የነበረም ነው፡፡ አንድን ነገር በሩቅ እያለ መዐዛው ሲያውድህ ወይም ቅርናትና ግማቱ ሲያጥወለውልህ በምናባዊ የስሜት ህዋስህ እየተሰማህ ስሜቱ ገና ላልተሰማቸው ልታስታውስና የማንቂያ ደወል ልታሰማ ትችል ይሆናል፡፡ ነገር ግን እንዳለመታደል ይሆንና ሰሚ ታጣለህ ወይም ከጉዳይ የሚጥፍህ አይኖርና እንዲሁ ደክመህ ትቀራለህ፡፡ የመጨረሻው መጨረሻ ሲመጣና በምናብህ የታየህ ነገር የሁሉንም ቤት መቆርቆር ሲጀምር ግን ቀዳሚው ዕይታህ እውነትና የማይቀርም መሆኑን አንተ ራስህም እንደሌላው እየተደመምክ ጊዜ ባለውሉን ታደንቃለህ፡፡ በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በየመን መታፈንና ለትግሬው ነፃ አውጪ ወያኔ በቅጽበት ተላልፎ መሰጠት ሳቢያ ሰሞኑን እያስተዋልነው ያለነው ሀገራዊ ክስተት ይህን ነው የሚመስለው፡፡
በባህላዊ ዘፈኖቻችን በአንደኛው ውስጥ የመጀመሪያውን ስንኝ ለጊዜው ዘነጋሁት እንጂ በርዕሴ ላይ የጠቀስኩትን የመሰለ ተከታይ ስንኝ አለ፡፡ የሚፈራ ነገር ጊዜ ይፍጅ እንጂ መድረሱ የማይቀር መሆኑን ይጠቁማል፡፡ እኔም የፈራሁት፣ ብዙዎች ሩቅ ተመልካች ኢትዮጵያውያንም የፈሩት፣ ቀደም ካለ ዘመን ጀምሮ በአንዳንድ ኢትዮጵያውያን የትንቢት መዛግብት ውስጥም የተቀመጠውና በእጅጉ የተፈራው ነገር በቅርብ ሊፈጸም እንደሆነ ከዳር ዳርታው እየተረዳን በመሆናችን የፈራነው ነገር ድሆ ድሆ ስለመምጣቱ ቅንጣት መጠራጠር አይገባም፡፡ ለምንድንስ ነው የምንጠራጠረው? እንኳንስ ዘረኛው የትግሬ መንግሥት ከሆዳምነታቸውና ከጨካኝነታቸው በስተቀር በአንጻራዊ ሁኔታ ለሀገራቸው አንድነትና ለሕዝባቸው ደኅንነት ይተጉ የነበሩ የቀ.ኃ. ሥላሴንና የአፄ መንግሥቱ ኃ/ማርያምን የመሳሰሉ ኢትዮጵያውያን መንግሥታትስ ጊዜያቸውን ጠብቀው ወደታሪክ መዝገብነት ተለውጠው የለም እንዴ? ታዲያ የወያኔን ወረደ መቃብር መዳረስ ለምን እጠራጠራለሁ? የወያኔ የባሕርይ አባቶች ናዚው ሂትለር፣ ፋሽስቱ ሙሶሊኒ፣ አምባገነኖቹ መንግሥቱና ሞቡቱ፣ ኢድ አሚንና ጋዳፊ ወዘተ. ተራቸውን እየጠበቁ ወደማይቀረው ሞት ተጉዘዋል፡፡ የመለስ ዜናዊ ወያኔም የማይቀርለትን ዕዳ ሊወጣ ቁልቁለቱን በከፍተኛ ፍጥነት እየተንደረደረ ነው፡፡ ውሃ ውስጥ ገብቶ እየሰመጠ የሚገኝ ሟች ደግሞ የሚያድነው እየመሰለው ፊላና ሣር እንዲሁም የሚንሳፈፍ የወፍ ላባ ሳይቀር ይጨብጣል፡፡ ሞቱ ታሪካዊና የማይቀር የሆነው ወያኔ ደግሞ የሚድን እየመሰለው ይጨብጠውንና ይለቀውን አጥቶ በሚያሳዝን የኅልውና ሁኔታ ውስጥ ይገኛል – ጣረሞታዊ ኅልውናውን ኅልውና ካልነው፡፡
እርግጥ ነው – ወያኔ በመሞት ላይ ነው ስል የነጋበት ጅብ ብዙ ምናልባትም ሊጠገን የማይችል እጅግ ብዙ ጉዳት ማድረሱ እውነት እንደመሆኑ ወያኔም በዚህ የአመሻሽ ሰዓቱ – በዚህ የጣዕረ ሞት ቅጽበቱ ለግምት የሚከብድ ጠባሳ እንደሚያስከትል በተግባር እያየነው ነው፡፡ ስለዚህም ትግልን በተቻለ መጠን በጥንቃቄ ማድረጉ ብዙ ኪሣራ ውስጥ ላለመግባት ጠቃሚ ነውና ልብ ያለው ልብ ይበል፡፡ ይህን ስልም የወያኔ ሞት ይቀራል ማለት እንዳልሆነ ላሰምርበት እፈልጋለሁ፡፡ የወያኔ ሞት ወያኔ ስለጠላው ወይም እኛ ስለወደድነው የሚቀር ወይም የሚመጣ አይደለም፤ ታሪካዊ ሞት ስለሆነ ማንም ሊያግደው የሚችለው አይደለም፡፡ የወያኔ ሞት በተቃዋሚዎች መጠንከር ወይም መልፈስፈስ የሚወሰን አይደለም፤ ሁሉም የራሱ ጊዜ አለውና ወያኔ ከየትም አቅጣጫ በሚነሣ ወጀብና ሕዝባዊ ዐውሎ ንፋስ ይገረሰሳል፡፡ ዕዙ ከፈጣሪ በመሆኑ፣ መነሻው የሕዝብ ዕንባና ደም በመሆኑ የወያኔ ኅልፈት በማንም ምድራዊ ኃይል አይስተጓጎልም፡፡ ማዘግየትና ማፋጠን ግን ይቻል ይሆናል፡፡ ስለሆነም የትግል ሥልትን አዋጭ በሆነ መንገድ መቀየሱ ጉዳዩ ይበልጥ ከሚመለከታቸውና የእምዬ ኢትዮጵያን ነፃነት ለማዋለድ ታሪክ ከመረጣቸው ዜጎች ብዙ ይጠበቃል፡፡ እርግጥ ነው – የኢትዮጵያን ነፃነት እውን ለማድረግ በትንሹ ኢትዮጵያዊነት እንጂ የድርጅት አባልነት የግድ እንዳልሆነም መገንዘብ ተገቢ ነው፡፡ ሀገር የጋራ ናት፤ ፓርቲና ቡድን ግን የግል ናቸው – ሃይማኖትም፡፡ በመሆኑም ሁሉም የቻለውን ያድርግ፡፡ (የጠምባሮ ብሄረሰብ ብሂል ናት – አንድ ሰው የሞላ ወንዝ ዳር ቆሞ ወንዙ እስኪጎድልለት ድረስ ይጠብቃል – ሊሻገር፡፡ በዚህ መሀል ግንዱንና ደንጋዩን እያንከባለለ ከሚወርደው ጎርፍ ላይ ያ ሰውዬ ጠላቱን ያያል፡፡ በደስታ በመሞላትም አክ ይልና ምራቁን አጠረቃቅሞ እጎርፉ ላይ እንትፍ ይላል፡፡ የርሱ ምራቅ በጎርፉ ላይ ተጨምሮ ጠላቱን “ጠራርጎ” እስከመጨረሻው የወንዙ መዳረሻ እንዲወስድለት መሆኑ ነው፡፡ ልክ ነው! እኛም የዚህን ሰው አርአያ መከተል ይኖርብናል፡፡ የዋህነታችንና ፍርሀታችን በቃል ለማይገለጽ ውርደት ዳርጎናልና፡፡)
በዚህን ወቅት የሥልጣን ሱስ ሰለባውን፣ የፍቅረ ንዋይ ምርኮኛውን፣ ሰው መሣይ ድንጋይ ራሱን፣ አደናጋሪውን፣ አዘጥዛጩን፣ አሽቃባጩን፣ አስመሳዩን፣ አድር ባዩን፣ ከርሳሙን፣ ቂጥኛሙን፣ ውርዴውን፣ ነቀርሣውን፣ … መጠንቀቅ ይገባል፡፡ በዚህ በተዘበራረቀ ማኅበረሰብ ውስጥ ማንን ከማን ለይቶ ማመንና አለማመን ስለሚከብድ ብዙ ጥንቃቄ ያስፈልጋል፡፡ በተረፈ የወያኔ ሞት ከላይ እንጂ ከታች ብቻ ስላልሆነ እውን መሆኑ የግድ ነው፡፡ በሥነ ቃሉም “እንዲህ ጨሶ ጨሶ የነደደ እንደሆን፤ ያመዱ ማፍሰሻ ሥርፋው ወዴት ይሆን፡፡” መባሉ ለዜህ ነው፡፡
ማን ያውቃል፡፡ የአንዳርጋቸው በዚህ ባልተጠበቀ ሁኔታ ውስጥ መገኘት ለበጎ ቢሆንስ? የርሱን መሰዋት ግዴላችሁም ብዙም አንጥላው፡፡ ስንዴ ካልሞተች ለሌሎች ስንዴዎች ትንሣኤ መነሾ አትሆንምና – ድል ያለ መስዋዕት እንደማይጣፍጥም ይነገራልና የአንዳርጋቸው በወያኔ ወጥመድ ውስጥ መግባት ፈጣሪ ወዶና ፈቅዶ ያደረገው ይመስለኛል፡፡ እርግጥ ነው “አታሞ በሰው እጅ ታምር ሲይዟት ታደናግር” እንዲሉ ነውና ይህ ክስተት በኔና ባንተ ቢሆን ሊከብደን ይችላል፡፡ ይሁንና አንዳርጋቸው በነዚህ ጭራቆች እጅ መግባቱ ለበጎ ነው የምልባቸው ብዙ ምክንያቶች አሉ፡፡ ይሄውና ለዓመታት ሲጎሻመጡና ዐይንህ ላፈር ሲባባሉ የነበሩ አንዳንድ ተቃዋሚዎች – በቡድንና በድርጅትም በግለሰብም ደረጃ – የአንድነት መንፈስ ያሳዩት በዚህ ሰሞን ነው፡፡ ወያኔዎች ለአገዛዝ እንዲያመቻቸው ባዘጋጁት የክፍፍል አባዜ ሳይዘናጋ ወይም በቋሚነትም ይሁን በጊዜያዊነት ወደጎን በመተውና ግንቦትና ሚያዚያ ሳይባባል ምድረ አበሻ ከጫፍ እስከ ጫፍ የተነቃነቀው በዚህ ሰሞን ነው – የሚያስቀና ነውና ያዝልቅልን፡፡ “የትም ብኖር ለካንስ ወያኔ ከፈለገ አንገቴን ጨምድዶ እንደፈለገው ሊያደርገኝ ይችላል” ከሚል ስሜት በመነሳት ይመስላል አበሻ ሁላ መከፋፈሏን እየናቀች ወደጋራ መድረክ የመጣችው በዚሁ ሰሞን ነው – እንዳንዳንዶቻችን ግምት ለጊዜያዊ የፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ሊሆን ይችላል ብለን ብንጠራጠርም፡፡ ሌላም ሌላም፡፡ እንደዚህ ሰሞኑ ትብብርና መተሳሰብ ቢሆን ኖሮ ወያኔዎች ወደደደቢታቸው ከተመለሱና ከናካቴውም ከከሰሙ በትንሹ 30 ዓመታትን ባስቆጠሩ ነበር – ግና የኛ ኃጢኣትስ በምን ሥርየትን ያግኝ? እንዴትስ ይከፈል? ሁሉም ነገር ለበጎ ነው፡፡ ከዚህ አንጻር ታዲያን የአንዳርጋቸው ጭዳነት ለመልካም ፍጻሜ ቢሆንስ? ፈጣሪ ሌላ መንገድ ከመፈለግ ይልቅ ይህኛውን የወዲያው መንስኤ (immediate cause) ፈቅዶትስ ቢሆን? አላውቅም፤ ግን እንዲህ ያለ ነገር ይሰማኛል – ስሜት የድርጊትን ያህል ከባድ ባይሆንም፡፡ በታሪክ ትምህርት ለአንድ ኹነት መነሾ ሁለት መሠረታዊ ምክንያቶች እንዳሉ ይነገራል – fundamental and immediate causes ይሏቸዋል – መሠረታዊና የወዲያው መንስኤዎች ልበላቸው፡፡ የአንደኛውን ይሁን የሁለተኛውን የዓለም ጦርነት ያስነሳችው በሰው ማሣ የገባች አንዲት ቀበጥ ዓሣማ እንደሆነች ሲነገር ሰምቻለሁ፡፡ ለአንድ የቦካ ቂም እውናዊ ትንሣኤ አንዲት ቀጭን ሰበብ ታስፈልጋለች ማለት ነው፤ የአንዳርጋቸው ግን ከቀጭንም በላይ እርፍ እሚያህል ነውና በቃላት ብቻ የሚያልፍ እርግማንና ቁጣ ሰቆቃን ከማባባስ ውጪ የሚፈይደው ነገር እንደሌለ መረዳት ይኖርብናል፡፡
አንዳርጋቸው በአረመኔዎቹ እጅ ከገባ በኋላ በደከመ አንደበት “blessing in disguise” ሲል ሰምቻለሁ፡፡ በወያኔዎቹ ትርጓሜ እንዲህ ማለቱ “መያዜ ዕረፍት ሰጥቶኛልና ከእንግዲህ እኔ እንዳረፍኩና ሰላም እንዳገኘሁ እናንተም አርፋችሁ በመቀመጥ ሰላማችሁን አረጋግጡ” ለማለት እንደፈለገ እንዲገባን የፈለጉ ይመስለኛል፡፡ እውነተኛውን ትርጓሜ ጊዜ ይነግረናል፡፡ አንዳርጋቸው ግን የቆርጦ ቀጥሎቹን ወያኔዎች ምኞት የሚያስተናግድ ንግግር እንደማያደርግ ከግምት የሚልቅ እምነት አለኝ፡፡ ለነገሩ እንደዚያም ቢሆን አይገርመኝም፡፡ ወያኔዎችን ለሚረዳ ሰው፣ አንድን ሰብኣዊ ፍጡር ከሰይጣንም በላይ ሰይጣን በመሆን እንዴት እንደሚያሰቃዩና በዘመናዊ መንገድ ሂፕኖታይዝ በማድረግም ጭምር ከአንድ አእምሮ ምን ዓይነት ግብኣት ጨምረው ምን ዓይነት መረጃ ሊያወጡ እንደሚችሉ እረዳለሁ፡፡ ዘመኑ በስይጣኔ (በስልጣኔ አላልኩም) እጅግ የተራቀቀ ነው፡፡ በአርትዖት (ኤዲቲንግ) መቁረጥ መቀጠሉ እንዳለ ሆኖ እንደፈረንጆቹ ከሆነ በአእምሮን መቆጣጠሪያ ዘዴ (ማይንድ ኮንትሮል ሲስተም) የአንድን ሰው አእምሮ ሙሉ በሙሉ በመቆጣጠር የፈለጉትን መረጃ ከትተው ሲያበቁ ሰውዬው ያንኑ እንዲናገር የማድረግ ሰይጣናዊ ችሎታ አላቸው፡፡ ደርግም በጊዜውና ቤት ባፈራለት የማሰቃያ መንገዶች “አልጋችን ሥር ታንክ ደብቀናል” የሚያስብል ወፌላላና የዘይት ጥብሳት እንደነበረው እናስታውሳለን – አለመታደላችን ግን ምን ያህል የበረታ ነው! ወያኔማ ከዚያ የሚብስ እንዴት አይኖረው! ለማንኛውም በበኩሌ የአንዳርጋቸውን ፈረንጃዊ ፈሊጥ ለኔ በሚስማማኝ መልኩ በመጋራት ይህ ሁኔታ ለኢትዮጵያ “mixed blessing” ነው እላለሁ፡፡ ከእንግዲህ መጨነቅ ለኛው ነው፡፡ አንዳርጌ ግዳጁን ተወጥቷል፡፡ ስለሱ ማላዘንም ይብቃ፡፡ በአንዳርጋቸው እጅ መዛል ምክንያት ከእጁ ያመለጠችዋን ባንዲራ ተረክቦ መታገል ይገባናል፡፡ ልቅሶና ዋይታ ሆድ ከማስባስና ወደኋላ ከመጎተት በስተቀር ማንንም አይጠቅምም፡፡ ሀበሻነትን ለጊዜው ገታ አድርገን ፈረንጅ እንሁንና ጥርሳችንን ነክሰን አቀበቱን እጅ ለእጅ ተያይዘን በኅብረት እንውጣ፡፡ ባይሆን ሁሉም የዚህ ቲያትር ተካፋይ የየራሱን ሒሳብ የሚያወራርድበትን ቀመር አዘጋጅቶ ማስቀመጥ ነው፡፡ የመንም፣ ወያኔም፣ … በዚህ ቆሻሻ ተግባር የተሳተፈ ሁሉም ፍጡር ዋጋውን እንደሚያገኝ በበኩሌ ጥርጥር የለኝም፡፡ የኢትዮጵያውያን ጊዜ ሲመጣ የ”ለለአሃዱ በበምግባሩ” ፍትህ ይበየናል፡፡
ወያኔዎች ጨካኞች መሆናቸውን እናውቃለን፡፡ በአንዳርጋቸው ላይ ምን ሊያደርጉ እንደሚችሉም በጣም ግልጽ ነው፡፡ ነገር ግን ማስታወስ የሚገባን ነገሮች አሉ፡፡ የትግራይ ወንበዴዎች ትግሉን ለተወሰነ ጊዜም ቢሆን ያኮላሹ መስሏቸው አንዳርጋቸውን ሊገድሉት ይችላሉ – ምድር ላይ ገና ባልተሞከሩ የማሰቃያ ሥልቶች ማሰቃየታቸው እንደተጠበቀ ሆኖ፡፡ አሰቃዩትም ገደሉትም ከእንግዲህ ዕዳው የነሱና የኛ እንጂ የአንዳርጋቸው አይደለም፡፡ አንዳርጋቸው ከዕዳው ነፃ ነው የምለው ሥራውን ጨርሷል በመባሉ አይደለም፡፡ በእጅህ የገባን ብርጭቆ ስትፈልግ መስበር፣ ሳትፈልግ ማስቀመጥ ያለብህ አንተ ስለሆንክ አንዳርጋቸውን እንደፈለጉ የማድረግ ዲያብሎሳዊ መብትና ሥልጣን ያላቸው ወያኔዎች ብቻ ናቸው፡፡ ለምን አስያዙት ብሎ መቆጣትም ሞኝነት ነው፡፡ እንዲያውም ቂልነት፡፡ አንዳርጋቸው ዓለምን የሚዞረው ለወያኔዎች ዕቅፍ አበባ ለማበርከት አለመሆኑ መታወቅ አለበት፡፡ ከዚህ አኳያ ለምን ያዙት ብሎ መናደድ ጉንጭ አልፋና ለትዝብትም የሚዳርግ ነው፡፡ የሚያናድደው የተያዘበት አኳኋን ነው፡፡ ያመኑት ፈረስ በደንደስ መጣሉ ነው እጅግ የሚያበግነው፤ ዓለም አቀፍ ህግ መጣሱ ነው የሚያንጨረጭረው፤ ሊያስቀሩት ይቻል በነበረ የአደጋ ሥጋት አጉል መስዋዕትነት መክፈሉ ነው የእግር እሳት፡፡ በጦርነት ቢሆን እሰዬው ነው – የአሁኑን ያህል ቁጭትና ንዴት የለበትም፡፡ ለዚያ ሰሞኑን ለደረሰው ጥፋት ደግሞ የአንድ ወገን ብቻ ሣይሆን የብዙ ወገኖች ጥፋት ይመስለኛል – ትምህርቱ ቆንጣጭና አስቆጪ መሆኑ ከፋ እንጂ ይህ ክስተት መማሪያ ነው፡፡ ደግሞም ከፍ ሲል ለመጠቆም እንደሞከርኩት የፈሰሰ አይታፈስምና ስህተትን በመከፋፈልና በመጸጸት ጊዜን ማባከን ተገቢ አይደለም፡፡ የሆነው ሆኖኣል – የሆነውም ሊሆን ግድ ስለሆነ መሆኑን ማመን ይገባል፡፡ የማይሆን ቢሆን ኖሮ ቀድሞውንም አይሆንም ነበርና፡፡ እናም ጉዞ ወደፊት እንጂ ወደኋላ የለምና ይልቁንስ የተሰዋው ወንድማችን አስተዋፅዖ ከግቡ እንዲደርስ እንጣር፡፡ ተሰዋ ስልም በርግጥም እስካሁኒቷ ሰዓት ተሰውቷል ለማለት ሳይሆን የወያኔ እጅ የገባ ሰው የድመት ምርኮኛ የሆነ ያህል ስለሚሰማኝ ነው፤ እንጂ ከንፍሮ ጥሬ ይወጣልና እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ አንዳርጋቸውም የነገን ጣይ ሊያይ የሚችልበት ጠባብ ዕድል ሊኖር ይችል ይሆናል – ወያኔዎች ማሰብ ከጀመሩ፣ አሁን ዘግይተውም ቢሆን በመጨረሻ ሰዓታቸው ወያኔዎች ሰው መሆን ከጀመሩ ይህም ቀላል ነው፡፡ ተያይዞ ከመጥፋት ቢያንስ ለትውልዳቸው ሊያስቡ ከፈለጉ እያንዣበበ የሚገኘውን የጥፋት ደመና ከወዲሁ ሊያስቀሩት ይችላሉ፡፡ እኔ ግን አይመስለኝም፡፡
ወያኔዎች ወደፊትን መመልከት የማይችሉ ደናቁርት መሆናቸው ከአንዳርጋቸው ሕይወት አንጻር ያሳዝነኛል፡፡ የሚያሳዝነኝ አንዳርጋቸው ሳይሆን የወያኔዎች ድንቁርና ነው፡፡ የሁልጊዜ ትምክህታዊ መርሆኣቸው “ማን ምን ያደርገናል? ተልባ ቢንጫጫ በአንድ ሙቀጫ…” የሚለው አፄያዊና ደርጋዊ ትዕቢታቸው ነው፡፡ አሁንና ከአሁን በኋላ ግን ይህ ትምክህት አይሠራም፡፡ ለሁሉም ጊዜ አለው፡፡ ለመፍራት ጊዜ አለው – ለመጀገን ጊዜ አለው፤ ተስፋ ለመሰነቅ ጊዜ አለው – ተስፋ ለመቁረጥ ጊዜ አለው፤ ለመለያየት ጊዜ አለው – ለመተባበር ጊዜ አለው፤ ለመጣላት ጊዜ አለው – ለመታረቅ ጊዜ አለው፡፡ ይህን ነባራዊ ዘመን የማይሽረው እውነት ቅዱሳት መጻሕፍትም ቀድመው አስቀምጠውታል፡፡ በአሁኑ ወቅት ለወትሮው በፈሪነትና በልዩነቶች ተከፋፍሎ በመራኮት ዘመን አመጣሽ ወያኔ ወለድ ጠባዩ ወያኔዎች ይፈርጁት የነበረው የኢትዮጵያ ሕዝብ ወደ ቀደመው አንድነቱ እየመጣና ቁጭቱን ለመወጣት መንገድ አመላካች ሙሤ እየፈለገ ነው፡፡ ስለዚህ አንዳርጋቸውን መግደል ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ እንደሚያመዝን እነሱ ባይገባቸው የምናውቅ ወገኖች ጠንቅቀን እናውቃለን – ይህን ስል እንዳይገድሉት በውስጠ ወይራ ለመለማመጥ አይደለም – ወያኔዎች ልምምጥና ልመና እንደማይገባቸው አውቃለሁ፤ ወያኔዎች ያሸነፉትን በመግደል የሚረኩ ጅሎች እንጂ አንድም የጀግንነትና የመሐሪነት መንፈስ እንደሌላቸውም አውቃለሁ፡፡ ጅብ ለማንም እንደማይራራ ወያኔም ከጅብ በበለጠ የራሱን ተጋዳዮች ሳይቀር እየቀረጠፈ ነው እዚህ የደረሰው፡፡ ጅብ እንኳን ጓደኞቹ ሲቆስሉና ሲሞቱ ነው አሉ እሚበላቸው፡፡ ወያሜዎች ግን አንድን ሰው ለመብላት በተቃዋሚነት መጠርጠርና በጠላትነት መፈረጅ ብቻ በቂያቸው ነው፡፡
ሴትዮዋ “መንግጌ አባስኩሽ” እንዳለችው ነው፡፡ የወያኔዎች የኅልውና ማስጠበቂያ ሥልቶች በሙሉ ታኝከው አልቀዋል – ባለፉት ሠላሳ ምናምን ዓመታት ዕድሜያቸው የመግዥያ ሥልቶቻቸውን አንድ በአንድ አኝከው በልተው ጨርሰዋቸዋል፡፡ መግደልም፣ ማሰርም፣ ማሰቃየትም፣… ሁሉም ፋሽኑ አለቀ፡፡ የሞተን ሰው የማትገድልበት፣ የሞተን ሰው የማታስርበት፣ የሞተን ሰው የማታሰቃይበት ጊዜ ሊመጣ እንደሚችል ማወቅ ይኖርብሃል – እንደዚያ ያለ ሰው ከሆንክ፡፡ እርግጥ ነው – ወያኔዎች የሚያሰማሯቸው የሕወሓት ወጠምሻ ድንጋይ ራሶች ሆዳቸው እስከሞላ ድረስ አንጎል የሚባል ነገር ስለሌላቸው ከመግደልና ከማሰቃየት ወደኋላ አይሉም – በዚያ ላይ እንዲያደፋፍሯቸው የሚጠቀሙባቸው አንዳንድ ንጥረ ነገሮች ሳይኖሩ እንደማይቀሩ እገምታለሁ – ለምሳሌ ሀሺሺንና ጫትን መጠጥንም የመሳሰሉ፡፡ ደግሞም ብዙ ትግሬ ካድሬዎች – ስታዘባቸው – ቂላቂል ናቸው፡፡ ለድርጅታቸው ያላቸው ታማኝነት የማምለክ ያህል ነው – ከዚያም በላይ፡፡ በየመጠጥ ቤቱ በጣራ መለስ ጩኸት ሲያውካኩ ስትሰማ – በዚያም ጩኸት ኢትዮጵያዊነትን የሚያራምዱ ወገኖችን እንዴት ሲሳደቡና ሲወርፉ ስታዳምጥ በርግጥም እነዚህ ሰዎች ወያኔ እስከወዲያኛው በሥልጣን ፀንቶ እንደሚኖር የሚያምኑና አድርጉ የተባሉትን ሁሉ ያለማቅማማት እንደሚያደርጉ ትገነዘባለህ – ተገንዝበህ ብቻ አታበቃም – ካዘንክባቸው በኋላ ታዝንላቸዋለህም፡፡ “አንድ ሰው ምን ያህል አእምሮው ከሥራ ውጪ ቢሆን ነው በሰው ስቃይ የሚደሰተው?” ብለህ ራስህን ስትጠይቅ የዓለም ወቅታዊ ቅርጽ ከሦርያ እስከ ሶማሊያ ፊትህ ላይ ድቅን ሊልብህ ይችላል – ሊያውም ለዘመናት አብሮ በኖረው ወገኑ ላይ፡፡ ችግሩ የሚከፋውና ተስፋህን የሚያሟጥጥብህ ደግሞ ድርጅታቸውን በጭፍን ስለሚወዱና – ይህም ለሆድና ለዘውጋዊ የዓላማ ጽናት ሲሉ ነው – ኢትዮጵያዊነትን ፈጽመው እንዲጠሉ ስለተደረጉ ከነዚህ ሰዎች ጋር መነጋገርም ሆነ መደራደር የማይቻል የማይሞከርም የመሆኑ መጥፎ አጋጣሚ ነው፡፡ ሰው ግን በስንት ይበደላል!
አንዳርጋቸው ቢገደል አፈር አያሟሽም፡፡ አንዳርጋቸውን ቢገድሉት አንድ ነገር ይቀርበታል፡፡ ያም በጉጉት ይጠብቃት የነበረችዋን የኢትዮጵያን ነፃነት ሊያይ አለመቻሉ ብቻ ነው፡፡ ወያኔዎች ቢገድሉት ይህን የአንዳርጋቸውን ጉጉት ባጭር ለማስቀረት ካላቸው ፍላጎት እንጂ ዕድሜያቸውን ለማርዘም የርሱ ሞት ጠቃሚ ሆኖ እንዳልሆነ እስካሁን ካላወቁት አሁኑኑ ሊያውቁት ይገባል- በቃ፤ እውነቱ ይህ ነው፡፡ እንጂ አንዳርጋቸውን በመግደል የኢትዮጵያን ነፃነት እናስቀራለን የሚል አስተሳሰብ አሁንም ካላቸው በርግጥም በዱሮው ጅልነታቸው እንደታሰሩ ናቸው ማለት ነው፡፡ የተቆረጠን ቀን የአንድ ሰው መሞት አለመሞት አይመልሰውም፡፡ አያድርግበትና ቢገድሉት እንዲያውም ኢትዮጵያ ትጠቀማለች፤ ወያኔ ግን ክፉኛ ይጎዳል፡፡ አንዳርጋቸው በአንዳርጋቸውነቱ ቢሞት ባይሞት ምንም ማለት እንዳልሆነ ግልጽ ነው – ወንድ ሲናገር ዛሬ ጧት ከኢሳት እንደሰማሁት አንዳርጋቸው በሕይወቱ የደላው ሰው አልነበረም – በሀገሩ ፖለቲካዊ ቀውስ ሳቢያ ከገሞራው ኃይሉ(ኃይሉ ገሞራው?) ብዙም ያልተሻለ ሕይወት ይመራ እንደነበር ተገንዝቤያለሁ፤ ኢትዮጵያን ያለ – ስለኢትዮጵያ አብዝቶ የተጨነቀ ተጠቅሞ አያውቅም – ምን ሩቅ አስኬደኝ … ነገን በተስፋ ሲጠብቁ ይህች ቅጽበታዊ ምድራዊ ዕድሜያቸው እየከዳቻቸው ያሉ በየሽርንቁላው ተወትፈው ቅዳሜን እሁድ ለማድረግ የሚታትሩ በርካታ ልጆች አሏት – ኢትዮጵያ፡፡ አንዳርጋቸው የሚለየው ጥሪውን ተቀብሎ የድርሻውን አበርክቷል – እናም አይቆጨውም፡፡
የርሱ ነገር መንጠልጠያው በትንሹ የሰባና የሰማንያ ሚሊዮን የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው፡፡ አንዳርጋቸውን ሲገርፉ ኢትዮጵያን እየገረፉ ነው፡፡ አንዳርጋቸውን ሲያሰቃዩ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያንን እያሰቃዩ ነው፡፡ የአንዳርጋቸውን ጥፍር ሲነቅሉ የኔንም ጥፍር እያወለቁ ነው – ልዩነቱ የኔ በስሜት ነው – የርሱ ግን በውነት ነው፡፡ ይህ ደግሞ የዞረ ድምር አለው፡፡ ዛሬ አንዳርጋቸውን የሚያሰቃዩ ሰዎች ደናቁርት ይሁኑ እንጂ እነሱም የሚሰቃይና የሚሞት ሰብኣዊ አካል ወይም ሰውነት አላቸው፤ ቤተሰብ አላቸው፤ ቀጣይ ትውልድ አላቸው፤ ሀብት ንብረት አላቸው፤ ባያምኑበትም ኢትዮጵያዊ ማንነትና ሥረ መሠረት አላቸው፡፡ ስለሆነም በነገይቷ ኢትዮጵያ በነሱና የነሱ በሆነ ነገር ላይ ሁሉ ምን ሊደርስ እንደሚችል ከአሁኑ ሊገምቱ ካልቻሉ በርግጥም ኅሊናቸው ታውሯል፤ አንጎላቸውም ተሰውሯል ማለት ነው፡፡ ዘመድ የሚያስፈልገው ይሄኔ ነው፡፡ መካሪ ያስፈልጋል፡፡ አንዳርጋቸውን መግደል ያዋጣ የነበረው ዛሬ አይደለም – ቀደም ሲል ቀረ፡፡ እርሱን ከመግደልም ይልቅ የዐዋቂዎችን ምክር ሳይንቁ ቢሰሙና ሥልጣን ከያዙ ጀምሮ እያደረጉ የመጡትን ዘግናኝ አፍራሽ ነገሮችን ባያደርጉ፣ ለሕዝብ ስሜት ቢገዙ፣ የሕዝብን ፍላጎት ቢያከብሩ አንድ አንዳርጋቸውንና ከርሱም በፊት ያረዷቸውን ሚሊዮን ኢትዮጵያውያንን ሳይረፈርፉ ከኢትዮጵያውያንና ከከራማዋ ጋር ታርቀው በቀላሉ በሰላም መኖር በቻሉ ነበር፡፡ አሁን ግን በጣም መሽቷል፤ ድንግዝግዝ ብሎባቸዋል – ከፈጣሪና ንጹሓን ፍጡሮቹ ጋር ደም ተቃብተው ከሰማዩም ከምድሩም ጋር ክፉኛ ተቀያይመዋል፡፡ አንዳርጋቸው ሌላ ኃጢኣትና ወንጀል ኖሮበት ሳይሆን በትንሹ የሚከተሉት ነገሮች እንዲወገዱ ነው የታገለው፡፡ እንደማሣረጊያ ከመቶ የትግሬ ወያኔ ጥፋቶች ዜሮ ነጥብ ዜሮ ዜሮ አንዱን ብቻ እዚህ ላይ ማስታወስ ፈለግሁ፡፡ ቀናና የመልካም ሥነ ምግባር ባለቤት የሆን ትግሬዎች በዚህ የወያኔዎች ዕኩይ ድርጊት ልናዝን እንጂ ባላደረግነው ነገር የቀያችን ልጆች ስላደረጉት ብቻ ልናፍር አይገባም፡፡ ክፉ ሥራና ኃጢኣት በዘርና በጎሣ አይተላለፍም፡፡ ሁሉም እንደሥራው እንጂ በጎጣዊ ማንነቱ ፍርድን አይቀበልም፡፡ እነዚህ ኢትዮጵያን ከእግር እስከራስዋ ወርረው እስከመቅኒዋ ድረስ እየመጠመጡ የሚገኙ ሰዎች ኅሊና ብሎ ነገር፣ ሀፍረት ብሎ ነገር፣ ይሉኝታ ብሎ ነገር አልፈጠረባቸውምና አንዳርጋቸውን ቆራርጠው ቢበሉት ለጊዜውና አሁን የአማርኛውን ጉድ “ጉድ!” ከማለት ውጪ ሌላ ቃል የለንም፡፡ የነገውን ግን አንድዬ ነው የሚያውቅላቸው፡፡
አዲስ አበባ ውስጥ የአንድ ቀበሌ ሥራ አስፈጻሚ ያደረገው ተዓምር ይህ ነው፡፡ ከበላዮቹ ለአንድ ሹመት አንድ ባለዲግሪ መርጠህ ላክ ይባላል፡፡ ይህ ሰው ባለዲግሪ ትግሬ ቢያፈላልግ ያጣል፡፡ ምሥጢሩን የተረዳ አንድ ከርታታ አማራ “እኔ የሚፈለገው ዲግሪ አለኝ አይደለም እንዴ ለምን አትልከኝም?” ብሎ ይጠይቀዋል፡፡ ምን መለሰለት መሰላችሁ – “ያንተን ዲግሪ ለሽንት ቤት ተጠቀምበት!”፡፡ ያ ቆፍጣና ካድሬ አንዷን ባለዲፕሎማ ትግሬ ላከና ዐረፈው፡፡ ትግሬ ሁን እንጂ፣ በዚያም ላይ ታማኝነትን ደርብበት እንጂ መማር አለመማርህ ዋጋ የለውምና ሥራ ለመያዝ በባለዲግሪዎች የሌሎች ዘውጎች ተቀጣሪ አሽከሮችህ ላይም ለመዘባነን የሚያሳስብህ ነገር የለም – ተዓምር ነው፤ ከተዓምርም በላይ፡፡ የዚህ ሁሉ ጎጠኝነት መንስኤ ሥራ በትክክል ተሠራ አልተሠራ ወያኔን የማያስጨንቀው መሆኑ ነው – የሚያስጨንቀው ፖለቲካውንና ጥቅሙን ከወያኔ ትግሬ ውጪ ሌላ ኢትዮጵያዊ መያዙ ነው፡፡ ያ ያንገበግበዋል፡፡ ኢትዮጵያ ማለት ትግሬ፣ ትግሬ ማለት ኢትዮጵያ ሆናልሃለች፡፡ በሁሉም የመንግሥት መ/ቤቶች በአዛዥ ናዛዥነት እንደልቡ የሚፈነጥዘው ትግሬ ወያኔ ነው፡፡ ሌላው ባይተዋር ነው – ጨዋ ኢትዮጵያዊ ትግሬም ጭምር፡፡ በተለይ አማራ ለዘበኝነትም የማይታመን ሆኖልሃል ወዳጄ! አማራ “የሥራውን ነው ያገኘው፤ እሰይ! እንኳን!” እንዳልል ይህ ዘውግ በዚህን (ወያኔዎች በሚያሳዩት ደረጃ) ያህል ድፍረትና በዚህን ያህል ክትሩን የለቀቀ ጀብድ ኢትዮጵያን በግሉ ተቆጣጥሮ የጋጠበት፣ ሌሎችን በዚህን ያህል ደረጃ ያዋረደበት አንድም የግል ተሞክሮም ይሁን ታሪካዊ የጽሑፍ ማስረጃ ላገኝ አልቻልኩም፤ እናም ለመፍረድ ተቸገርኩ፡፡ እዚያው አጠገባቸው ስለምኖር ይህን አውቃለሁ፡፡ ፍርድ ለራስም ነውና በምለው ነገር እርገጠኛነቴን አትጠራጠር፡፡ እንዲህ የምለው ለዲያስጶራው እንጂ የዚሁማ የዚሁ ነው፡፡ እዚህ ያለውማ ነጋ ጠባ የተለማመደውን መራር እውነት እኔ ላረዳው ይቻለኛልን?
አንድ የኢሕአዴግ አባል የሆነ አማራ ያደረገው ተዓምር ይህ ነው፡፡ ይህ ሰው እንዲህ የሚል የቅጥር መመሪያ በውስጥ ማስታወሻ ይደርሰዋል፡- “ ስትቀጥር 50 በመቶ ትግሬ፣ 25 በመቶ ደቡብ፣ … 1 በመቶ አማራ …” ይህ አባል ትግሬ መስሏቸው ሊሆን እንደሚችል መገመት ይቻላል – ብዙዎቹ ትግሬ ካድሬዎች ይሉኝታ ስለሌላቸው ጅሎች መሆናቸውን ልብ ይሏል፡፡ ያ የኢሕአዴግ አማራ ካድሬ ብልጥ ነበርና አመልካቾች ሲመዘገቡ አማራ ነን የሚሉትን በጆሯቸው ጠጋ እያለ “ሃድያ ነኝ ብለህ ተመዝገብ”፣ “ጠምባሮ ነኝ በል”፣ “ኮንሶ ብለህ ተመዝገብ” … በማለት ምድረ አማራን በደቡብ ስም ከደቡቦቹ ጋር እያዛነቀ ቀጠረ አሉ፡፡ ምን ያድርግ፤ ጅብ ከሚበላህ በልተኸው ተቀደስ ይባል የለም? በዚህ መልክ ብቀጥል አውሎ ያሳድረናል፡፡ ይህንን ዐይን አውጣ የወያኔ ዕኩይ ተግባር ለማስተካከል መሞከር ሽብርተኛ ካሰኘ የነሱ ምን ሊባል እንደሚችል ራሳችሁ ገምቱ፡፡ ጎበዝ፣ ኢትዮጵያዊነት እንዲህ እንደወያኔ ከሆነ ባፍንጫየ ይውጣ፡፡ ከእንስሳትም ወረዱብኝ፡፡ …
ተዓምረ ወያኔ ከዚህም ከዚያም
• ኃ/ማርያም ደሳለኝ የትሮይ ፈረስ ሆኖ በውስጡ ያሉት እነሐጎስና እነግደይ ናቸው፡፡ ኃ/ማርያም ከሁለቱ የኢትዮጵያ መንግሥታት የአንደኛው አሻንጉሊት ነው – ኢትዮጵያ የኅቡዕና የግልጽ ሁለት መንግሥታት እንዳላት የማያውቅ መቼም የለም – የነጎይቶምና የነአብረኸት የመጋረጃው በስተጀርባ መንግሥትና የነደቻሳና የነስንሻው የምስለኔና እንደራሴ የውክልና መንግሥት፡፡ የኃ/ማርያም አሻንጉሊትነት “ኢትዮጵያ ከደቡብ ሕዝቦች የመጣ ጠ/ሚኒስትር አላት” የሚል ቅባት በተለይ ለደቡቡ ሕዝብና ለውጪው ዓለም ማደናገሪያነት መቀመጡ ነው፡፡ እንጂ ስለኢትዮጵያ የወቅቱ አስተዳደር ቅንጣት አያውቅም – እንዲያውቅም አይደረግም፤ ለታይታ ካገለገለ እርሱ ምን ቤት ሆነና! ግን ወግ አይቀርምና በሚዲያቸው “ጠ/ሚኒስትር ኃ/ማርያም ከቻይናው አቻቸው ከቺንግቹዋ ቹንግ ጋር ተወያየ፡፡ ጠ/ሚኒስትር ኃ/ማርያም ስለታላቁ የህዳሴ ግድብ ከግብጹ አቻቸው ከፕሬዚደንት አልጉልቤ ሲሲ ጋር ተነጋገሩ …” ይባልልኛል፡፡ ቂቂቂቂቂ ….. አለች ያቺ ጋዜጣ ጽሑፋዊ ሳቋ አምልጧት፡፡ የቃሉ አጠራር በጠያፍነቱ ምክንያት ባያስነውረኝ ኖሮ ኃ/ማርያምን “ኮንዶም ነው” ባልኩና ደስ ባለኝ፡፡
• የአደባባይ ምሥጢር፡፡ መከላከያ፣ ውጭ ጉዳይ፣ ፖሊስ፣ ደኅንነት፣ ጉምሩክ፣ የመንግሥት ባንኮችና ኢንሹራንሶች፣ መብራት ኃይል፣ ቴሌ፣ የትምህርት ተቋማት፤ ገቢና ወጪ ንግዶች፣ የግንባታና የልማት ድርጅቶች፣ ፋብሪካዎች፣ ሆስፒታሎች፣ ክፍለ ከተማዎች፣ ወረዳዎች፣ አነስተኛና ጥቃቅኖች፣ ሱቆች፣ መጋዘኖች፣ ማከፋፈያዎች፣ ፋብሪካዎች፣ ኢንዱስትሪዎች፣ ወዘተ. ሙሉ በሙሉ በትግሬ ወያኔዎች ቁጥጥር ናቸው – የሌሎች ዘውጎች አባላት በታዛዥነት መኖራቸው አያስገርምም – ከተላላኪነትና ከእንደራሴነት የዘለለ ሚና የላቸውም ግን፡፡ ኢትዮጵያ በትግሬ ወያኔዎች የወለድ አግድ ማነቆ ሥር ናት፡፡ ተናደድ፤ መናደድ ባንተ አልተጀመረም፡፡ ስትናደድ ወደ ለውጥ የሚያመራ መንፈስ ይመጣልሃል – ምናልባትም ጥሩ መንፈስ፡፡
• በግል ትምህርት ቤቶች በውድ ዋጋ ከሚማሩ ተማሪዎች መካከል በግምት ከመቶ 95 የሚበልጡት ወላጆቻቸው ትግሬዎች ወይም ኢሕአዴግ ከሚባለው የወያኔ ዋሻ አንዳች ፍርፋሪና ዳረጎት የሚጣልላቸው ውዳቂ ዜጎች ናቸው፡፡ ደግሞም ለትምህርት ዋጋ የማይሠጡ ደናቁርት ናቸው፡፡ ልጆቻቸው ቢማሩ ባይማሩ ደንታቸው አይደለም፡፡
• በየትም ሥፍራ በተለይም በአዲስ አበባ ከሚሠሩ ህንፃዎችና የልማት አውታሮች ውስጥ አሁንም በግምት ከ80 ከመቶው የሚበልጡት የትግሬዎች ናቸው፡፡
• አዲስ አበባና መቀሌ ልዩነታቸው ፍጹም እስከሚጠፋ ድረስ ሁሉም የአዲስ አበባ ንግድ ቤቶች በትግሬ ወያኔዎች ቁጥጥር ሥር ሊገቡ የቀራቸው ጊዜ ግፋ ቢል ከአሁን በኋላ አሥር ዓመት ቢሆን ነው – እንዲያውም ከዚያም ያንሳል፡፡ የትም ሂዱ፣ የትም ግቡ ባለሱቁና ባለመኪናው ባለሀብቱና ባለቀብራራ ኑሮው ትግሬ ነው፤ ገንዘቡን የሚመነዝረው ትግሬው ነው፤ ለሚስቱ ብቻ ሳይሆን ለየውሽማውም ሳይቀር የሀገራችንን ሀብት መኪናና ቤት በመግዛት የትም የሚረጨው ትግሬው ነው፤ ሕዝብ ቆሼ ተራ ሀብታም በጣለው ፍርፋሪ ላይ ሲራኮትና ዜጋ በየመንገዱ ወድቆ በርሀብ አለንጋ ሲገረፍ ወያኔ ትግሬዎች በልጆቻቸው የልደት ቀን በሚሊዮን የሚገመት ገንዘብ ለድግስና ለስጦታ ያወጣሉ – ድንቁርና ከዚህ በላይ ካለ ንገሩኝ፡፡ ዜጎች በርሀብ እየወደቁ፣ ተማሪዎች በርሀብ ምክንያት መማር እያቃታቸው በምሣ ሰዓት በየትምህርት ቤቱ ኮሪደር እየተዘረሩ፣ የለማኙ ቁጥር ከመጽዋቹ ቁጥር በልጦ ኢትዮጵያ የቧጋቾች ሀገር ሆና ጥቂት ወያኔ ትግሬዎችና አንፋሽ አከንፋሾቻቸው ለራሳቸው እንደምትመጥን አድርገው በፈጠሯት አዲሲቷ የወያኔ ኢትዮጵያ ውስጥ ልዩ ምድረ ገነት ፈጥረዋል፡፡ የሌሎች ዘውጎችን ነጋዴዎች የቤት ኪራይ በመቆለልና ከአቅማቸው በላይ የሆነ ግብር በመጣል ከንግዳቸው አባርረው፣ መኖሪያ ቤታቸውንም እንዳመቺነቱ በዘረፋና ወይም በግዢ ነቅለውና ፈንቅለው የአሁኑ የአዲስ አበባ ጠረን ትግሬ ትግሬ የሚል ሆኗል፡፡ ቦሌም ግባ ጉለሌ “ጥሩ ጥሩ ለትግሬ” በሚል ሥውር ዐዋጅ ሌላው ከሥሩ ተፈንቅሎ ለስደትና ለማራሪነት ሲዳረግ ወያኔዎች ገብተው ይዝመነመኑበታል – ይህንን ሁሉ ግፍ የማይቆጥርና ዕዳን የማያስከፍል ፈጣሪ የለም የምትሉ ከሆነ እኔ የለሁበትም፡፡ የፍርድ ቀን ከመምጣቱ በፊት ወያኔ ትግሬዎች ሆይ አቅል ጀባ!
• ምሥኪን ዜጎች ብሶታችንን እንዳንናገር እንኳ ንግግርን፣ አስተሳሰብንና ሃሳብ ማውጠንጠንን ራሱን በሽብርተኝነት የሚያሳስር ወንጀል እንደሆነ አስደርገው በወኪሎቻቸው የመንግሥት ወያኔ ትግሬዎች አማካይነት በሚያስወጧቸው የወሮበሎች ህግጋት በቁማችን መቀመቅ ሰደውናል፤ እንዳንታሰር እንፈራለን – ስለምንፈራም ፀጥ ረጭ እንላለን፤ ፀጥ ረጭ ስንልም ወደንና ፈቅደን የምንገዛላቸው ይመስላቸዋል፡፡ ገደብ የለቀቀውን “ትግስታችንን”ም እንደፍርሀት በመቁጠር እላያችን ላይ ይጸዳዱብናል፡፡ የመጸዳዳታቸው ውጤት የሆነው ክርፋትና ጥምባት ግን ፈጣሪን አስቆጥቶት ይሄውና … ቆይማ ብቻ፡፡ አሁን ምን አስቀባጠረኝ!
• ሌላው ዜጋ በልዩ ልዩ ዘዴ ያፈራው ሀብት እንኳን ቢኖረው በሰቀቀንና በፍርሀት ተጀቡኖ በሁለተኛና ሦስተኛ ዜጋነት ነው የሚኖረው – ያሳዝናችኋል፡፡ አንገቱን ቀና አድርጎ እንደልቡ የሚኖረው ደንቆሮ ትግሬ ብቻ ነው፡፡ ዕድሜ ለወያኔዎች ሩቅ ተመልካች ትግሬ ሳይቀር ነገን በማሰብ አቀርቅሮ እንዲኖር የተገደደበት ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡ ሌት ከቀን የሚዝናናው፣ በመኪናው ውስጥ በሚከፍተው የሙዚቃ ድለቃ በደረቅ ሌሊት ሕዝብን እንቅልፍ የሚነሳው፣ በየቡና ቤቱ እየዞረ ትግርኛ ካልተከፈተልኝ በማለት ሌላውን ዘፈን በነፍጠኛነት የሚፈርጀውና የሚያስፈራራው ጠግቦ እየዘለለ የሚገኘው ትግሬ ወያኔና አሽከሮቹ ናቸው፡፡ የሚገርመው ጠጪዉና ተዝናኙ ትግሬ ብቻ ነው ተብሎ በአዋጅ የተነገረ ይመስል በየመዝናኛውና በየምሽት ክበቡ የሚከፈተው ዘፈን ከሞላ ጎደል ትግርኛ ብቻ ነው፡፡ ትግርኛ ካልከፈታችሁ ቡና ቤታችሁ ይዘጋል የተባለ ይመስል አዳሜ ከገዢው ወገን ጋር የተዛመደ እየመሰለው የሚከፍተው ሙዚቃ ትግርኛ ብቻ የሚሆንበት አጋጣሚ ሞልቷል፤ ሁሉም ነገር የብሔር ተዋፅዖ በሚለው የወያኔ አስመሳይ ፍልስፍና እየተመራ(ከስልሳ የጦር ጀኔራል ስልሳውንም ትግሬ አድርገው ሲያበቁ እኮ ነው – አያስቁም? ድንቄም ተዋፅዖ!) ለምሳሌ የሞቀ ኦሮምኛ ተከፍቶ በምትጨፍርበት ሠርግ ላይ ሳታስበው ድንገት ትግርኛ ወይም ወላይትኛ ሊከፈት ይችላል – ያኔ የውዝዋዜ ሥልትህን በቅጽበት ትቀይርና በኩኑ ከማሆሙ ነባር ኢትዮጵያዊ ብሂል አንተም አለውድ በግድህ ሰሜነኛ ወይም ደቡብኛ ውዝዋዜውን ታስነካዋለህ – በአቅጣጫና በቁጥር ስያሜዎች አለቅን እኮ፡፡ አለዚያ “ይህን አይወድም፣ ይህን ይነቅፋል ወይ ይጠላል” በሚል ኢመደበኛ ግምገማ የሰው ዐይን ውስጥ ልትገባ ትችላለህ – በዚያም ሰበብ የምታጣው ነገር ሊኖር ይችላል፡፡ እስከዚህን የወረድን ሕዝብ ሆነናል – በዘፈን ምርጫ ሰውን መገምገም የሚዳዳባት ሀገር፡፡ እዚህ ላይ ትግርኛ መከፈቱ አስከፍቶኝ ሳይሆን ራስን ያለመሆን ጠባይ እየጎላ መምጣቱ ግን አስገርሞኝ ነው፡፡ በየትምህርት ቤቱማ ብታዩ ታሪኩ ብዙ ነው፡፡ በየቦታው የምትሰሙት ሙዚቃ አስመሳይነትን እንጂ እውነተኛ ፍላጎትንና ምርጫን አያመለክትም፡፡ ገበያን ለመሳብ ብቻ እንዴት የአንዲት ከተማ ቡና ቤቶች ተመሳሳይና የተሰለቹ ዘፈኖችን አንድን ወቅት እየጠበቁ (የስካርና የመዝናኛ) ይከፍታሉ? ወረተኝነት ከምን ጊዜውም በላይ እየተስፋፋ ነው፡፡ ነገ ደግሞ የሽናሻ መንግሥት ቢመጣ ቡና ቤቱ ሁሉ ሽናሽኛ ዘፈን እየለቀቀ ካለተዝናኙ ፍላጎት ሊያደነቁረው ነው ማለት ነው፡፡ ትንግርቱ ብዙ ነው፡፡ ይህን የምለው በጥራዝ ነጠቅ የማውቃት የሥነ ልቦና ትምህርት ግንዛቤየ እየታወሰችኝ ሰዎች የሚያደርጓቸውን ነገሮች ለምን፣ እንዴትና መቼ እንደሚያደርጉ ወይም እንደማያደርጉ የጫረብኝ አስጠሊታ ምስል ነው፡፡ ሰው ግን ምን ያህል አስመሳይ ፍጡር ነው!? ምን ነካን? ብንወርድ ብንወርድ እስከዚህ እንውረድ?
• አዲስ አበባ ውስጥ ከሚዝመነመኑ ግሩም አውቶሞቢሎች ከአሥሩ በትንሹ ሰባቱ የትግሬዎች ናቸው ቢባል ስህተቱ ለኩነኔ አያደርስም፡፡ የንግድ መኪናውን ብትመለከትም እውነቱ ከዚህ ብዙም አይለይም፡፡ ትግሬ ግን ከኢትዮጵያ ሕዝብ አጠቃላይ ብዛት ግፋ ቢል 8 በመቶ ቢሆን ነው፡፡ የጥንቱን ስድስት በመቶውን አሁን እርሱት – አዲስ አበባ ላይ የሚርመሰመሰው ወያኔ ብቻውን ከአምስት በመቶ የሚያንስ አይመስለኝም – ለቁጥር ያለኝ ቀረቤታ እንደበውቀቱ ሥዩም እስከዚህም ቢሆንም፡፡ አማራው ቀንሷል – ትግሬው ጨምሯል፤ በምናውቃቸውም በማናውቃቸውም ምክንያቶች የተነሣ፡፡ ዘር ማብዣ ማዳበሪያ ወደትግራይ – ዘር ማምከኛ በስሪንጋ የሚሰጥ ብልቃጥ መርዝ ወደአማራ፡፡ ታሪክ ይፋዊ የምሥክርነት ቃሉን ሊሰጥ በቋፍ ላይ ነውና በትግስት እንጠብቅ፡፡ አለ ገና – ብዙ ነገር ይታያል፡፡ ዕድሜና ጤና መለመን ነው፡፡ አንድዬ የሚሳነው ነገር የለምና ያቆየን፡፡ የምመክራችሁ እንድትናደዱ ነው፤ ስትናደዱ ወደመፍትሔው ትጠጋላችሁ፡፡ አሪቬዴርቺ፡፡"